Home Featured ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሲጀመር ተማሪዎች ኃላፊነት ለመውሰድም ይዘጋጁ ብሏል።
FeaturedNews & UpdatesUncategorized
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሲጀመር ተማሪዎች ኃላፊነት ለመውሰድም ይዘጋጁ ብሏል።
written by adminJanuary 1, 2024
0
SHARES
በአማራ ክልል የሚገኙ 10 የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት 2 ሳምንታት መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ እንደሚጀምሩ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል።
የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ ኮማንድ ፖስት፣ የፀጥታ አደረጃጀቶች፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የ10 ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ፀጥታ አካላት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተከታታይ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቶ የውይይቶቹ የመጨረሻው ክፍል ሐሙስ ከተደረገ በኃላ ነው ውሳኔው የተላለፈው።
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) ምን አሉ ?
– ከመስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተማሪዎችን ለመቀበል ተዘጋጅተን የነበረ ቢሆንም፣ በክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ሳቢያ ተሰናክሏል።
– በእኛ በኩል የዝግጅት ክፍተት የለብንም።
– በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቁጥጥር ሥር የሆነ የፀጥታ ሁኔታ አለ። ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆነም የፀጥታ ሁኔታ አለ። ከእኛ ውጪ በሆነው ጉዳይ ላይ ምንም ማድረግ አንችልም። ምንም ማድረግ ባልቻልንበት ሁኔታ የሰው ልጅ ጠርቼ አንድ መጥፎ ነገር ቢከሰት ምንድነው የምለው ? የሚለውን ተማሪዎችም፣ ወላጅንም ታሳቢ አድርገን ተማምነን ይቆይ የሚል አቋም ስለነበረን በዚህ ምክንያት ነው እስካሁን ቀስ እያልን የመጣነው።
– የመማር ማስተማሩ እንዲጀመር በነበረው ውይይት ሒደት አቅደን የነበረው ተመራቂ ተማሪዎችን ወደ የትምህርት ግቢያቸው ማስገባት ነበር።
– እስካሁን ባለን ልምድ ግጭቶች እዚህም እዚያም ሊቀሰቀሱ ይችላሉ። ቀጣይነታቸው ግን ብዙም አይደለም። አንድ ቀን ወይ ሁለት ቀን መስተጓጎል ሊፈጠር ይችላል ከዚያ ግን ያበቃል።
– ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ተጠርተው ሲመጡ ታሳቢ ማድረግ ያለባቸው ጉዳዮች አሉ ፤ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ሊያጋጥሙ የሚችሉ ዕክሎችን ከግምት በማስገባት ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው።
– ተማሪውም፣ ወላጅም፣ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብም እንደ አገር የሚመለከታቸውም አንድ ላይ ሆነን መደበኛ ትምህርት መጀመር አለብን ብለን ወስነናል።
– የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተቋማቸው ከልደት (ገና) በዓል በኋላ ባሉት ቀናት ለተማሪዎቹ ጥሪ ያደርጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ መሆኑን ያሳውቃል።