ደቡብ ኮሪያዊው ባለሃብት ቼይ ታኤ-ዎን ለፈቷቸው ባለቤታቸው 1 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍሉ በፍርድ ቤት ታዘዙ።
ባለሃብቱ በጥሬው እንዲፍሉ የተፈረደባቸው የገንዘብ መጠን በደቡብ ኮሪያ ታሪክ በፍቺ ምክንያት የሚከፈለው ትልቁ ገንዘብ ሆኗል።
እኚህ ባለጸጋ ሮህ ሶ-ያንግ ከሚባሉት ባለቤታቸው ጋር የተለያዩት ከትዳር ውጪ በመሰረቱት የፍቅር ግንኙነት ልጅ መውለዳቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነው።
የባለሃብቱ ጠበቆች ፍርድ ቤቱ የቀድሞ ሚስት ጉዳይን ብቻ ስለተመለከተ ይግባኝ እንላለን ብለዋል።
ሁለቱ ጥንዶች ከተለያዩ በኋላ እአአ 2022 ላይ ሚስት 500 ሚሊዮን ዶላር እንዲሰጣቸው ወስኖ ነበር።
ይህን ውሳኔ ሰጥቶ የነበረው ፍርድ ቤት ሮህ አቅርበውት የነበረውን የቼይ ኩባንያ የጋራ ባለቤትነት ጥያቄን ውድቅ አድርጎ ነበር።
ሮህ ጉዳዩን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወሰዱት በኋላ ችሎቱ ሚስት ኤስኬ ግሩፕ በሚባለው የቼይ ኩባንያ ውስጥ ድርሻ ሊኖራቸው ይገባል ብሏል።
የሴዉል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንት ሐሙስ በዋለው ችሎት ሮህ ሶ ያንግ እና ቼይ ታኤ-ዎን ለ35 ዓመታት በትዳር መቆየታቸውን ገልጾ ሚስት የኩባንያው ድርሻ ሊኖራቸው ይገባል ብሏል።
ፍርድ ቤቱ “የኤስኬ ግሩፕ ዋጋ እና የቼይ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲጨምር ሮህ እንደ ሚስት አስተዋጽእኦ አበርክተዋል ብሎ መገመት ይቻላል” ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም ሮህ የቀድሞ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ሮህ ታኤ-ዎ ልጅ መሆናቸው ኤስኬ ግሩፕ ከለላ እንዲያገኝ እድል አግኝቷል ብሏል።
ፍርድ ቤቱ የቼይ አጠቃላይ ንብረትን ወደ 4 ትሪሊየን ዎን የገመተ ሲሆን፤ ለቼይ ሦስት ልጆችን የወለዱት ሮህ ከአጠቃላይ ንብረቱ 35 በመቶ ይገባቸዋል ብሏል።
ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ቼይ ትዳር ውስጥ እያሉ ሌላ ልጅ መውለዳቸው የሮህ ስሜትን መረበሹን፤ በአንጻሩ ቼይ በድርጊታቸው ምንም አይነት መጸጸት አለማሳየታቸውን ገልጿል።
ኤስኬ ግሩፕ ለኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ግብዓት የሆኑ ሴሚኮንዳክተር በማምረት በዓለማችን ቀዳሚው ነው። ከዚህ በተጨማሪ በቴሌኮም፣ በኬሚካል እና ኢነርጂ ላይ የተሳተፈ ኩባንያ ነው።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ ( ቢቢሲ ዜና )