ቻይና የቲክቶክን የአሜሪካ ድርሻ ለኢላን መስክ ለመሸጥ አስባለች የተባለው ወሬ “ልብ-ወለድ ነው” ሲል ኩባንያው አስተባበለ።
ብሉምበርግ የቻይና ባለሥልጣናት ቲክቶክ በአሜሪካ ያለውን ድርሻ ለዓለማችን ቱጃሩ ሰው ለመሸጥ እያጤኑ ነው የሚል ዘገባ አስነብቦ ነበር።
የአሜሪካ መንግሥት ቲክቶክን ሊያግድ የቀሩት ቀናት ጥቂት ናቸው።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛዎች በአውሮፓውያኑ ጥር ይታገዳል ስለተባለው ቲክቶክ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ቲክቶክ ከዚህ ቀን በፊት የዩናይትድ ስቴትስ ክንፉን መሸጥ አለበት፤ ካልሆነ ዕጣ ፈንታው መታገድ።
ቲክቶክ በተደጋጋሚ የአሜሪካ ገበያውን ለሌላ ባለሀብት አሳልፎ መሸጥ እንደማይፈልግ ሲያስታውቅ ከርሟል።
“መቸም ልብ-ወለድ በሆነ ዜና ላይ አስተያየት እንድንሰጥ አይጠበቅም” ሲሉ የቲክቶክ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ብሉምበርግ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ሰዎች ባገኘው መረጃ መሠረት የቻይና ባለሥልጣናት ቲክቶክን የኤክስ ባለቤት ለሆነው ኢላን መስክ ለመሸጥ አቅደዋል ይላል።
የቀድሞው ትዊተር የአሁኑ ኤክስ ከቢቢሲ አስተያየት ተጠይቆ ምላሽ አልሰጠም።
ኢላን መስክ የተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ የቅርብ አጋር ነው። ትራምፕ በአውሮፓውያኑ ጥር 20 በዓለ ሹመታቸው ይከበራል።
ባለፈው ወር ትራምፕ እሳቸው ሥልጣን እስኪይዙ ድረስ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የቲክቶክን መታገድ እንዲያዘገየው ጠይቀው ነበር። ምክንያታቸው ደግሞ “ፖለቲካዊ መፍትሔ” ለመፈለግ ጊዜ ያሻኛል ነበር።
ትራምፕ የቲክቶክ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ሹ ዢ ቺውን ፍሎሪዳ በሚገኘው ማራላጎ የተለባ ሪዞርታቸው አግኝተው አናግረውታል።
ሰኞ ዕለት ሁለት ዲሞክራት ሕግ አውጭዎች ኮንግረሱ የቲክቶክን መታገድ እንዲያዘገየው ጠይቀዋል።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች ባለፈው ሳምንት በነበረው ችሎት ላይ ቀነ ገደቡን ተከትለው ቲክቶክን እንደሚያግዱት አስታውቀዋል።
የባይደን አስተዳደር እንደሚለው ቲክቶክ ለአሜሪካ ድርጅት ካልተሸጠ በቻይና መንግሥት ለስለላ እና ለፖለቲካዊ ብዝበዛ ሊውል ይችላል።
ኩባንያው በተደጋጋሚ ይህን ክስ ያስተባበለ ሲሆን ቲክቶክ በአሜሪካ እንዳይሠራ ማገድ የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት የሚጥስ ነው በማለት ይከራከራል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ፡– (ቢቢሲ)