ክሪስቲያኖሮናልዶየባይናንስማስታወቂያበመሥራቱየ1 ቢሊዮንዶላርክስተመሠረተበት Leave a comment

የእግር ኳስ ኮከቡ ክሪስቲያኖ ሮናልድ ግዙፉ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ የሆነው ባይናንስን በማስተዋወቁ 1 ቢሊዮን ዶላር ክስ ተመሥርቶበታል። ክሱ እንደሚጠቁመው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ባይናንስን በማስተዋወቁ ኪሳራ የደረሰባቸው ሰዎች አሉ። በዚህ ምክንያት ለደረሰው ኪሳራ ተጫዋቹ 1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ካሳ እንዲከፍል ተጠይቋል።

የሮናልዶን ኩባንያም ሆነ ባይናንስን አስተያየት እንዲሰጡ ያቀረበው ጥያቄ እስካሁን ምላሽ አላገኘም። በአውሮፓውያኑ ኅዳር 2022 ባይናንስሲአር7” ሲል የሰየማቸውን ኤንኤፍቲ የተሰኘ ስብስብ በማስተዋወቅ ይህን የገዙለዓመታት ድጋፋቸውሽልማት ያገኛሉ ብሎ ነበር።

ኤንኤፍቲ ማለት በዲጂታል መልክ ብቻ የሚገኝ፤ የሚሸጡ የሚለወጥ ንብረት ነው። በጠቅላላው ሰዎች የአንድ ፎቶ አሊያም ቪድዮ ባለቤት ይሆናሉ ማለት ነው። ይህን መግዛት፣ መሸጥም መለወጥ የሚችሉት በዲጂታል ይዘቱ ብቻ ነው።

ሲአር7” የሮናልዶ ስም የመጀመሪያዎቹ ቃላትና የማሊያ ቁጥሩ ያለበት መለያው ሲሆን ከአልባሳት ጀምሮ እስከ ሽቶ ድረስ በዚህ ስም ለገበያ የሚያቀርብ ሲሆን ከዓለማችን ሀብታም ስፖርተኖች አንዱ እንዲሆን አስችሎታል። ሮናልዶ በማሕበራዊ ሚድያ ገፆቹ በሠራው ማስታወቂያ ኤንኤፍቲንተጠቅመን እግር ኳስን አንድ ደረጃ እናሳድጋለንሲል ሰዎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ አበረታትቷል።

ኅዳር 2022 እኒህ ኤንኤፍቲ የሚባሉ የማይዳሰሱ ቁሶች ለገበያ ሲቀርቡ ዝቅተኛ ዋጋቸው 77 ዶላር ነበር። ነገር ግን ከአንድ ዓመት በኋላ ዋጋው ወደ 1 ዶላር አሽቆልቁሏል። ክሱን ያቀረቡት ሰዎች ሮናልዶ ከባይናንስ ጋር በሠራው ማስታወቂያ ምክንያት ሰዎች ይህን በተመለከተ የሚያደርጉት የበይነ መረብ አሰሳ “500 በመቶ ጨምሯልይላሉ።

ባይናንስ የተሰኘው ግዙፉ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ ኬይመንድ አይላንድ በተሰኘው ደሴት የተመዘገበ ነው። እንደዩናይትድ ስቴትስ ሴኪዩሪቲስ ኤንድ ኤክስቸንጅስኮሚሽን ከሆነ ይሄን ጉዳይ የሚያስተዋውቁ ታዋቂ ሰዎች የአሜሪካን ሕግ መከተል አለባቸው። የኮሚሽኑ ኃላፊ ጌሪ ጄንስለር እንደሚሉትታዋቂ ሰዎች ይሄን ኢንቨስተመንት ሲያስተዋውቁ ምን ያክል እንደተከፈላቸው ለሕዝቡ የማሳወቅ ግዴት አለባቸው።ነገር ግን ክሱ እንደሚለው ሮናልዶ ምን ያክል እንደተከፈለው ማሳወቅ ሲኖርበት ይህን ሳያደርግ ቀርቷል።

ሮናልዶ እና ባይናንስ የተሰኘው ኩባንያ አሁን በጋራ ሌሎች ዕቅዶች እንዳሏቸው ተጫዋቹ በቅርቡ በማሕበራዊ ሚድያ ገፁ ባሰፈረው ማስታወቂያ ገልጧል። ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ፍትሕ መሥሪያ ቤት ኩባንያው በፈፀመው ጥፋት ምክንያት 4.3 ቢሊዮን ዶላር እንዲቀጣ ማዘዙ የሚታወስ ነው። መሥሪያ ቤቱ፤ ባይናንስ በዓለም ዙሪያ ያሉ ተጠቃሚዎች ሕግ ሲተላለፉ ማስቆም አልቻለም፤ ወንጀለኞችና ሽብርተኞች ይህንን ዕድል ተጠቅመውበታል ሲል ይከሳል።

የባይናንስ ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ቻንግፔንግ ዣዎ ሕገወጥ ገንዘብ ማዘዋወር እንደነበር አምነው ከሥልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው ተነስተዋል። የአሜሪካው ሜጀር ሊግ ቤዝቦል፣ ፎርሙላ 1 እና ሜርሴዲስ ቤንዝ የተሰኙት ተቋማትም እንዲሁ ኪሳራ የገጠማቸውን ክሪፕቶዎች በማስተዋወቅ ተከሰዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop