” የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ይሰጣል ” – ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ Leave a comment

የ2016 ዓ.ም 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ” ፈተናው ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ ነው ” ብለዋል።

” በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን ይወስዳሉ ” ሲሉ አሳውቀዋል።

ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ከበደ በበኩላቸው  ፤ ” ፈተናው በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው ” ብለዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አመልክተዋል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ይጀመራል ብለዋል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ(@tikvahethiopia )

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop