በኤፍ ኤ ዋንጫ በ10 ተጫዋቾች ለመጨረስ የተገደደው ዩናይትድ በኤምሬትስ ስታድየም አርሰናልን በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።
ጨዋታው በፍፁም ቅጣት ምት የተጠናቀቀ ሲሆን ጆሹዋ ዘርክዚ የማሸነፊያውን ኳስ ከመረብ በማገናኘት የአርሰናልን የዋንጫ ሕልም አጨልሟል።
የዩናይትዱ ዲዮጎ ዳሎ በሁለተኛ ቢጫ ከሜዳ መሰናበቱን ተከትሎ ዩናይትድ በ10 ተጫዋቾች ጨዋታውን አጠናቋል።
በ52ኛው ደቂቃ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ባስቆጠረው ጎል አማካይነት ዩናይትድ ጨዋታውን እየመራ ነበር።
ዳሎ ከሜዳ የተሰናበተው በ61ኛው ደቂቃ ነው። ከሁለት ደቂቃ በኋላ አርሰናል በጋብርኤል ጎል አቻ ማድረግ ቻሉ።
የመሐል ዳኛው አንድሩ ማድሊ የዩናይትዱ ተከላካይ ሃሪ ማጓየር የአርሰናሉ አጥቂ ካይ ሀቨርትዝ ላይ ጥፋት ፈፅሟል በማለት ለመድፈኞቹ ፍፁም ቅጣት ምት ሰጡ።
የፍፁም ቅጣት መሰጠቱን ተከትሎ የሁለቱ ቡድኖች ተጫዋቾች ለተወሰነ ደቂቃ ያክል ዱላ ቀረሽ ፍትጊያ ውስጥ ገብተው ነበር።
የአርሰናሉ አምበል ማርቲን ኦዴጋርድ የመታውን የፍፁም ቅጣት የዩናይትዱ ግብ ጠባቂ አልታይ ባይንዲር መልሶታል።
የሚኬል አርቴታ ቡድን በዴክላን ራይስ እና በሀቨርትዝ አማካይነት ጨዋታውን ማሸነፍ የሚያስችላቸው አጋጣሚ ቢያገኙም አስደናቂ ሆኖ ባመሸው ባይንዲር ከሽፎባቸዋል።
የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ “የሳትናቸው ኳሶች የማይታመኑ ናቸው” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
“ጨዋታውን በብዙ ዕጥፍ ማሸነፍ ሲገባ ከውድድሩ ተሰናብተናል። ሰዎች የሚመዝኑን ደግሞ በዚህ ነው” ሲል አሰልጣኙ አክሏል።
90 ደቂቃው 1 አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ተጨማሪ 30 ደቂቃዎች ቢታከሉም አርሰናል የዩናይትድን ተከላካይ መስመር ጥሶ መግባት አልቻለም።
በተጨማሪው 30 ደቂቃም ቢሆን መድፈኞቹ የቀያይ ሰይጣኖቹን በር መክፈት ባለመቻላቸው በፍፁም ቅጣት እንዲለያዩ ሆኗል።
በፍፁም ቅጣቱ ምቱ የአርሰናሉ ካይ ሀቨርትዝ ሲስት ሁሉም የዩናይትድ ተጫዋቾች በማስቆጠራቸው አርሰናል ከኤፍ ኤ ዋንጫ ፉክክር ውጭ ሆኗል።
አርሰናል ባለፉት አራት የውድድር ዘመናት ሶስት ጊዜ በሶስተኛው ዙር ከኤፍ ኤ ዋንጫ ተሰናብቷል።
አዲሱ የዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ባለፈው ታኅሣሥ ወደ ኤምሬትስ መጥተው ቢረቱም አሁን ግን ተጠናክረው የተመለሱ ይመስላሉ።
ዩናይትድ ባለፈው እሑድ ከእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ መሪ ሊቨርፑል ጋር በነበረው ጨዋታ 2 አቻ ተለያይቶ ለውጥ እያመጣ እንደሆነ አስመስክሯል።
በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ ብቻ ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤ ለተጨማሪ መረጃ ድህረ ገጻችንን ይጎብ/ኙ። https://ethio-amazon.com/
ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon
ምንጭ፡– (ቢቢሲ)