የዘመናዊ አውሮፓ ሕብረት አባት የሚባሉት ዣክ ደሎር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ Leave a comment

የዘመናዊው አውሮፓ ሕብረት ቀማሪ የነበሩት የቀድሞው የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ዣክ ደሎር በ98 ዓመታቸው አረፉ።

በአውሮፓ ሕብረት ሃገራት ወጥ የገበያ ሥርዓት እንዲዘረጋ እንዲሁም ሰዎች፣ ምርቶችና አገልግሎቶች ያለምንም ገደቡ እንዲንቀሳቀሱ ያደረጉ ሰው ነበሩ።

በአውሮፓውያኑ ከ1985 እስካ 1995 ፕሬዝደንት ሆነው ያገለገሉት ደሎር የአህጉሪቱ መገበያያ የሆነው ዩሮ እውን እንዲሆን አግዘዋል።

ነገር ግን ጥምረት በማይፈልጉ በተለይ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ባሉ ሰዎች ዘንድ ግለሰቡ ብዙም ተቀባይነት አልነበራቸውም።

የደሎር ልጅ ማርቲን ኦብሪ አባቷ ፓሪስ በሚገኘው ቤታቸው ረቡዕ ጠዋት በሰላም ማረፋቸውን ይፋ አድርጋለች።

የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑዔል ማኽሮን ደሎርን አወድሰው “ጠንካራ ሃገር መስራች እና የአውሮፓ ቀማሪ”ሲሉ አድንቀዋቸዋል።

ፈረንሳዊው ዴለር ከአውሮፓውያኑ 1981 እስከ 84 የሃገራቸው የገንዘብ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።

“ቁርጠኝነቱ፣ ሐሳቦቹ እና የሞራል ልዕልናው ለሁላችንም ትልቅ አርአያ ሊሆን የሚገባው ነው” ብለዋል ማኽሮን።

“ለሥራው እና ጥሎት ላለፈው ነገር ላደንቀው እወዳለሁ፤ የቤተሰቦቹን ሐዘን ደግሞ እጋራለሁ።” ሲሉም ሐዘናቸውን ገልጸዋል።

ደሎር የአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ሆነው ሶስት ጊዜ አገልግለዋል። ይህ ከሌሎች ፕሬዝደንቶች የሥልጣን ዕድሜ ረዘም ያለ ነው።

የወቅቱ የኮሚሽኑ ፕሬዝደንት ኧርስላ ቮን ደር ሌየን “አውሮፓን ጠንካራ ያደረገ ባለራዕይ” ሲሉ ውዳሴያቸውን ገልጠዋል።

የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ቻርልስ ማይክል በበኩላቸው “ታላቅ ፈረንሳያዊ እንዲሁም ታላቅ አውሮፓዊ” ሲሉ የአውሮፓ ሕብረትን ያዘመኑትን ግለሰብ አድንቀዋል።

ሶሻሊስቱ ፈረንሳዊ ደሎር ከጦርነቱ በኋላ ጥምረት ያስፈልገናል ብለው በፅኑ የሚያምኑ ግለሰብ ነበሩ።

ወጥ ገበያ እና ዩሮ እውን ከማድረጋቸው ባለፈ ሸንገን የተሰኘው ከአንዱ ሃገር ወደ ሌላው በነፃ የመንቀሳቀስ ሐሳብ እና ኢራስመስ የተሰኘው የተማሪዎች ልውውጥን አስተዋውቀዋል።

ነገር ግን በወቅቱ ለነበረው የማርጋሬት ታቸር ወግ አጥባቂ የዩኬ ገዥ ፓርቲ ወደ ፌዴራል አውሮፓ መቀላቀል የሚዋጥ አልነበረም።

በ1989 ደሎር ያመጡትን የወጥ ገበያ እና የአንድ መገበያያ ሐሳብ ታቸር ተቀባይነት የሌለው ሲሉ ገልጸውት እንደነበር ይታወሳል።

በማርጋሬት ታቸር ዘመን ሥልጣናት የካቢኔ አባል ሆነው ያገለገሉት ሎርድ ክላርክ ጠቅላይ ሚኒስትሯ የደሎርን የወጥ ገበያ ሐሳብ ቢቀበሉትም ፖለቲካዊ ሕብረት መፍጠሩን አይስማሙበትም ነበር ሲሉ ለቢቢሲ ይናገራሉ።

በ1995 ከአውሮፓ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንትነታቸው ሲወርዱ የፈረንሳይ ፕሬዘደንት እንዲሆኑ ብዙዎች ቢጎተጉቷቸውም ደሎርን ግን ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

የፌዴራሊስት ሐሳብ አቀንቃኝ የሆኑት ደሎር ከብሬግዚት በኋላ በሰጡት አስተያየት በአውሮፓ ያለው ሕዝባዊነት እንደሚያሰጋቸው ተናግረው ነበር።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want