ዶናልድ ትራምፕ በታሪካዊው የክስ ሂደት በቀረቡባቸው ክሶች በጠቅላላ ጥፋተኛ ተባሉ Leave a comment

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታሪካዊ በሆነ የክስ ሂደት በቀረቡባቸው ክሶች በጠቅላላ ጥፋተኛ ተባሉ።

ፕሬዝዳንቱ ከንግድ መዝገቦች ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በቀረቡባቸው 34 ክሶች በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል።

በአሜሪካ ታሪክ በሥልጣን ላይ ያለም ይሁን ከሥልጣን የወረደ ፕሬዝዳንት በወንጀል ክስ ጥፋተኛ ሲባል ትራምፕ የመጀመሪያው ናቸው።

የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው ትራምፕ ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም. የቅጣት ፍርድ ይተላለፍባቸዋል ተብሏል።

ፍርድ ቤቱ ስድስት ሳምንታት በዘለቀው ችሎት ላይ ከ22 ሰዎች ምስክርነትን ሰምቷል። ከእነዚህ መካከል የቀድሞ የልቅ ወሲብ ተዋናይት ስቶርሚ ዳንኤልስ ትገኝበታለች።

ዳንኤልስ ከትራምፕ ጋር የወሲብ ግንኙነት መፈጸሟን እና ከ2016ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት ስለጉዳዩ ላለማውራት ተስማምታ ከትራምፕ ጠበቃ 130ሺህ ዶላር መቀበሏን ገልጻለች።

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጠበቃ ማይክል ኮሀን ፍርድ ቤት ቀርቦ በትራምፕ ትዕዛዝ ክፍያውን መፈጸሙን አምኗል።

ሕዳር 2017 ላይ በሚካሄደው የአሜሪካ ጠቅላላ ምርጫ ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው ዳግም ዋይት ሃውስ ለመግባት በዝግጅት ላይ ያሉት ትራምፕ፤ የክሶቹ መነሻ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች ናቸው ሲሉ ቆይተዋል።

12 ዳኞች ለሳምንታት የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምረው፤ ለሁለት ቀናት ከመከሩ በኋላ ትራምፕ በቀረቡባቸው ክሶች ጠቅላላ ጥፋተኛ ናቸው ብለዋል።

ትራምፕ ከፍርዱ በኋላ የዳኞች ስብስብን የሚመሩትን ዳኛ መርቻን አጥቅተዋል። የቀድሞ ፕሬዝዳንት ውሳኔው “አሳፋሪ” ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዛሬ አርብ ከሰዓት በኋላ በማንሃተን ትራምፕ ታዎር ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

ከትራምፕ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆነው ዊል ሻርፍ ለፎክስ ኒውስ ሲናገር ይግባኝ ለመጠየቅ “ያሉንን አማራጮች በሙሉ እየተመለከትን ነው” ብሏል።

ሌላኛው የትራምፕ ጠበቃ ደንበኛቸው ፍትሃዊ የፍርድ ሂደት አልተሰጣቸውም ብለዋል።

ጠበቃው የቀድሞ የትራምፕ ጉዳይ አስፈጻሚ እና ጠበቃ የነበረው ማይክል ኮሀን የትራምፕን ሕይወት ለማመሰቃቀል አልሞ የተነሳ በመሆኑ ምስክር ሆኖ ችሎት ፊት መቅረብ አልነበረበትም ብለዋል።

ከውሳኔው በኋላ ማይክል ኮሀን በሰጡት አስተያየት በፍርድ ቤቱ የተላለፈው ውሳኔ የጠበቁት መሆኑን ተናግረዋል።

“በመጨረሻም እውነት አሸንፏል። . . . ተጠያቂነት ሰፍኗል፤ ይህ አሜሪካ በአሁኑ ሰዓት በትክክል የሚያስፈልጋት ነገር ነው” ሲሉ የቀድሞ የትራምፕ አጋር የአሁኑ ባላንጣ ማይከል ኮሀን ተናግረዋል።

ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ በቀጣይ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የጆ ባይደን ተፎካካሪ ሆነው የሚቀርቡትን ግለሰብ እንዴት ሊጎዳ እንደሚችል የጠራ ነገር የለም።

ከፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላ የባይደን የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ባወጣው መግለጫ ትራምፕን በትክክል ማሸነፍ የምንችለው ችሎት ላይ ሳይሆን በድምጽ መስጫ ወረቀት ነው ብሏል።

የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን በበኩሉ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ ለምርጫ ቅስቀሳ ሬኮርድ በሆነ የሕዝብ ቁጥር በዲጂታል አማራጮች የገንዘብ ድጋፍ እየተቀበልን ነው ብሏል።

በድህረ ገጻችን ኢትዮ አማዞን በመግባት የሚፈልጉትን እቃ ማዘዝ  ብቻ  ሳይሆን የርስዎንም እቃዎች መሸጥ እንደሚችሉ ስናሳውቅዎት በደስታ ነው ። ለማስታወቂያ ወይንም ለመግቢያ ምንም ክፍያ አይጠበቅብዎትም፤  ለተጨማሪ መረጃ   ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ። https://ethio-amazon.com/

ለበለጠ መረጃ ሊንኩን በመንካት የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ!https://t.me/ethioamazon

ምንጭ ( ቢቢሲ ዜና )

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Cart

Your Cart is Empty

Back To Shop

የሚፈልጉትን ይዘዙን

Order what you want